Song Lyrics

ጓዳችንን አጽዳ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
ስርዓትህን ንቀን ቃልህን አቃለን መንፈስህ ሲወቅሰን ሁሌ እንሰማለን ሥጋ ብቻ ሆነን በአመፅ ተውጠናል እራስን መመርመር ፍፅም አቅቶናል አዝ፦ በከፍታ ስፍራ በሰማይ ያለኸው ምንም አይሳንህ ሁሉን ቻይ የሆንከው ልብን ኩላሊትን የምትመረምረው ጌታ ሆይ ጓዳችንን አፅዳ አጥበህ አስተካክለው ያኔ ስትልከን ጦርእቃህን ሰጥተህ ኃይል በኃይል አድርገህ ሞገስ አከናንበህ ከጦር ሜዳው ወጥተን ድልን ሰጥተኸናል ዛሬ ግን ወዮልን ጠላት ስቆብናል አዝ፦ በከፍታ ስፍራ በሰማይ ያለኸው ምንም አይሳንህ ሁሉን ቻይ የሆንከው ልብን ኩላሊትን የምትመረምረው ጌታ ሆይ ጓዳችንን አፅዳ አጥበህ አስተካክለው እንደ ቀድሞ መስሎን እንዋጋ ብንል በብዙ ለማጥመድ መረቡን ብንጥል ከንቱ ልፋት እንጂ ምርኮ ከየት ይምጣ ግራ ተጋብተናል በከንቱ እሩጫ አዝ፦ በከፍታ ስፍራ በሰማይ ያለኸው ምንም አይሳንህ ሁሉን ቻይ የሆንከው ልብን ኩላሊትን የምትመረምረው ጌታ ሆይ ጓዳችንን አፅዳ አጥበህ አስተካክለው አሁን ተረድተናል ኃጢአት አድርገናል በትዕቢት ፍላጻ አስለቅሰሃል በእርማችን ምክንያት ፊትህ ከብዶብናል ጌት ሆይ ታረቀን ማረን ብለንሃል አዝ፦ በከፍታ ስፍራ በሰማይ ያለኸው ምንም አይሳንህ ሁሉን ቻይ የሆንከው ልብን ኩላሊትን የምትመረምረው ጌታ ሆይ ጓዳችንን አፅዳ አጥበህ አስተካክለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection