መዋረዳቸውን አይተህ አንተ ይቅር በላቸው የቤትህን ልጆች አንተ ሰብረሀቸው ትዕቢታቸው ቀርቶ በትህትና ልባቸው እንባቸውን ሲያፈሱስ ለአንተ አየኋቸው አዝ፦ ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ እኔነቴ ቅርቶ ጸጋህ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ሽረህ ትህትና አልብሰኝ (2x) ጌታ ዘወትር መሰበርን ሽቼ አብዝቼ እጮሃለሁ ሌተቀን ተግቼ እስከመቸ ድረስ ሕይወቴ እንዲህ ደርቆ እኖራለሁ ጌታ ልምላሜ አርጐ አዝ፦ ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ እኔነቴ ቅርቶ ጸጋህ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ሽረህ ትህትና አልብሰኝ (2x) የመሰበር ፍላጐቴ ግለቱ ሳይበርድ ሰማዬችን ከፍተህ ምነው ብትወርድ ጉጉቴን ፈትነህ እባክህ ስበረኝ ትሁትና ታዛዥ መሆን አስተምረኝ አዝ፦ ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ እኔነቴ ቅርቶ ጸጋህ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ሽረህ ትህትና አልብሰኝ (2x) የራሴን ማንነት ያኔ በርግጥ እረዳለሁ የውስጥ ዓይኔ በርቶ አብዝቼም አያለሁ በፍፁም ግልጽነት ስምህን አውጃለሁ በበረከት ሙላት አስከብርሃለሁ አዝ፦ ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ እኔነቴ ቅርቶ ጸጋህ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ሽረህ ትህትና አልብሰኝ (2x)