አዝ፦ ዘመኑ ፈጠነ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን መከራ አስቡ ሰዓቱ ሊሞላ በቅርብ ነው ያለው መለከት ሊነፋ በቅርብ ነው ያለው ነገሩ ሊያከትም በቅርብ ነው ያለው ጌታም ከተፍ ሊል በቅርብ ነው ያለው አዝ፦ ዘመኑ ፈጠነ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን መከራ አስቡ ሰማያት ሲከብዱ ደመናው ሲጠቁር ምድራችን ስታምር ነገር ሲቀያየር ምን አዚም ኖረብን እንዳናይ ጊዜ አጥሮን ተው ነቃ እንበል እናቁም አንቅልፍን አዝ፦ ዘመኑ ፈጠነ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን መከራ አስቡ ሰው ሲተራመስ ሞትን ለመሳለም ከአምላክ ተለይቶ ለኃጢያት ሲታመን ጠቢቡ እንኳን ሲስት በሰይጣን ሲታለለ ተነሱ አንናገር ለነፍስ እንታገል አዝ፦ ዘመኑ ፈጠነ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን መከራ አስቡ እርሱ ያልሞተ እራሱን ያልከዳ ጌታ የማይገዛው ለኃጥያት ያልታገለ በምኑ ይመስክር ልቡ ይንቀጠቀጣል ዋጋም ክፈል ሲባል ትቶ ይፈረጥጣል አዝ፦ ዘመኑ ፈጠነ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን መከራ አስቡ