በበረታው ክንድ በበረታችም እጅ በጌታ መዳኑን ከሞት ከሲዖል እንደምን ዘንግቶ ሰው ያጉረመርማል ወንድሙን ለመውደድ እጁን ይዘረጋል አዝ፦ ስጋ ነፍሱን ዘርቶ አመጽ አቆጥቁጦ ትህትና ተረስቶ የትዕቢት ኃይል ፈሶ ፍቅርን ገደል ከቶ ጥላቻን ለማንገሥ ጥርሱን ይስል ጀመር ሰው ለመነካከስ አንተ ግን ጌታ ሆይ ምህረትህን አፍስስ (2x) ስፍራውን ለቆ ሲሄድ ለመጉደፍ ሲቸኩል ትህትናውን አውልቆ ለሞት ሲንቀለቀል እዪት ያንን ዝንጉ ቃል ኪዳኑን ሲያፈርስ በአመጻው ምክንያት ፍቅርን ሲያቀዘቅዝ አዝ፦ ስጋ ነፍሱን ዘርቶ አመጽ አቆጥቁጦ ትህትና ተረስቶ የትዕቢት ኃይል ፈሶ ፍቅርን ገደል ከቶ ጥላቻን ለማንገሥ ጥርሱን ይስል ጀመር ሰው ለመነካከስ አንተ ግን ጌታ ሆይ ምህረትህን አፍስስ (2x) አንተን እየፈራሁ ቀኑን ሁሉ ልኑር ትህትናም አይራቀኝ አልነፈግህ ፍቅር እጅህ እንዳይመታኝ አጉል ደፋር ሆኜ መተረቻ እንዳልሆን በሃፍረት ተሸፍኜ አዝ፦ ስጋ ነፍሱን ዘርቶ አመጽ አቆጥቁጦ ትህትና ተረስቶ የትዕቢት ኃይል ፈሶ ፍቅርን ገደል ከቶ ጥላቻን ለማንገሥ ጥርሱን ይስል ጀመር ሰው ለመነካከስ አንተ ግን ጌታ ሆይ ምህረትህን አፍስስ (2x)