Song Lyrics

የሰራልኝን ድንቅ

Pastor Tesfaye Gabisso
Chrsitian Teshagere
አዝ፦ የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ በዓለት እግሬን ኢየሱስ ቀድሞ ምህረቱን አብዝቶ ተዓምራትን ደግሞ አሳየኝ አምላኬ የከበረ ነገር እንደዚህ ሊመራኝ ወደ ፃድቃን አገር (2x) አዝ፦ የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ በቀኝ በግራዬ አድፍጦ አድብቶ መልካም መሰል አጥፊ ወጥመዱን ዘርግቶ ጌታ ግን ሲያድነኝ በጦር ተደራጅቶ ዲያብሎስ ሊያጠቃኝ ነበር ተሰናድቶ (2x) አዝ፦ የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ እርሱ ቅጥር ሲቀጥር በእምላኬ እየዘለልኩ ወጥመድ ሲዘረጋ እኔም እያመለጥኩ በእኔ ብርታት ሳይሆን በጌታ እየታመንኩ ሩጫ ቀጥላለሁ ሁሉን እያሸነፍኩ (2x) አዝ፦ የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ በዘለዓለም መድህን ከጥልቁ ወጥቼ ከእናት ከአባት ዘመድ የሚበልጥ አግኝቼ በአህዛብ መሃከል ለርሱ ዘምራለሁ የከበረ ሥሙን አመሰግናለሁ (2x) አዝ፦ የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection