አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁኝ በጨለማ ብቀመጥ እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል ስለዚህ ስለዚህ በእኔ ደስ አይበልህ የወይኑ ፍሬ ተለቅሞ እንደቀረው ቃርሚያ ደርቄ ቆሜያለሁ እኔ ከበረከት በስቲያ የሃዘን እንጉርጉሮዬን የምሬት ለቅሶዬን በአምላኬ ፊት እለቃለሁ እንዲያያት ሕይወቴን አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁኝ በጨለማ ብቀመጥ እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል ስለዚህ ስለዚህ በእኔ ደስ አይበልህ በእግዚአብሔር ላይ ኃጥያትን ሰርቻለሁና ቁጣው ለክፋቴ ሆኖ ነዶብኛልና ወደ ብርሃን እስኪያወጣኝ እታገሳለሁኝ ከውስጡም እስኪምረኝ ድረሰ ጠብቀዋለሁኝ አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁኝ በጨለማ ብቀመጥ እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል ስለዚህ ስለዚህ በእኔ ደስ አይበልህ በእኔና በአምላኬ መሃል የሚኖረውን ጉዳይ ኢየሱስ ይፈፅመዋል የመሰረቱ ድንጋይ ስለዚህ ጠላቴ ወግድ ጌታ ይገስጽህ አሁንም ቢሆን ልጁ ነኝ ተረዳ ከልብህ አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁኝ በጨለማ ብቀመጥ እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል ስለዚህ ስለዚህ በእኔ ደስ አይበልህ ለዘለዓለም አይቆጣም ምህረትን ይወዳል የጠላቴን ምኞት ቆርጦ ደስታውን ያቆማል የውርደት ማቄ ተቀዶ ነጭ ልብስ ለብሼ ዳግም ዘምራለሁ ለእርሱ ክንዱን ተንተርሼ አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁኝ በጨለማ ብቀመጥ እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል ስለዚህ ስለዚህ በእኔ ደስ አይበልህ