አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ የነፍሴ መድኃኒት የሰላሙ ንጉሥ ኢየሱስ ኢየሱስ ና ሕይወቴን ፈውስ ወደ እኔ ጩህ እኔም እመልሳለሁ ታላቁንም ነገር ለአንተ አሳይሃለሁ በቃልህ ስላልከኝ እንዲህ እጮሃለሁ እንድትፈውሰኝ ሥምህን ጠራለሁ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ የነፍሴ መድኃኒት የሰላሙ ንጉሥ ኢየሱስ ኢየሱስ ና ሕይወቴን ፈውስ በድካም ማዕበል ሕይወቴ ተከፍቶ በሚሰብር በትር ክፉኛ ተመቶ የታመቀው ስቃይ ልብን እየጣሰ እንባን አስክትሎ ወደ አንተ ደረሰ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ የነፍሴ መድኃኒት የሰላሙ ንጉሥ ኢየሱስ ኢየሱስ ና ሕይወቴን ፈውስ አልጥልህም ብለህ ከቶም አለቅህም የገባህልኝ ቃል አልተዘነጋኝም እኔ ፈዋሽህ ነኝ ብለህ የፈወስከኝ ከጉስቁልናዬ ና ዛሬም አድነኝ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ የነፍሴ መድኃኒት የሰላሙ ንጉሥ ኢየሱስ ኢየሱስ ና ሕይወቴን ፈውስ ሰባራውን ጠጋኝ የፈረሰውን አዳሽ ፈዋሽ አንተ ነህ የእንባዬ አባሽ ሰዎች ያላዩትን ቁስሌን ያየህልኝ አንተ ብቻ እኮ ነህ ዛሬም ያለህልኝ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ የነፍሴ መድኃኒት የሰላሙ ንጉሥ ኢየሱስ ኢየሱስ ና ሕይወቴን ፈውስ