Song Lyrics

ስብራቴ

Pastor Tesfaye Gabisso
Chrsitian Teshagere
እግሮችም የሉኝም ፊትህ የምቆምበት ዓይኖችም የሉኝም አንተን የማይበት የጠራኸኝ አምላክ ውርደቴን ተመልከት ከገባሁበት ማጥ አውጣኝ በአንተ ምህረት አዝ፦ ስብራቴ የማይፈወስ ይመስላል መደኃኒቴ አንተ ግን ምን ይሳንሃል ምህረትህ ካለ ማጉረምረም ምን ይጠቅመኛል በእጅህ ውስጥ መውደቅ ኦ እጅግ ይሻለኛል ከአንተ የተሰወረ ምን አለ ጌታ ሆይ ፍፁም ሳይገለጽ ተደብቆ የሚቆይ የልቤ መርማሪ የእኔ ውስጥ አዋቂ ምሬቴን ይቅር በል የነፍሴ ጠባቂ አዝ፦ ስብራቴ የማይፈወስ ይመስላል መደኃኒቴ አንተ ግን ምን ይሳንሃል ምህረትህ ካለ ማጉረምረም ምን ይጠቅመኛል በእጅህ ውስጥ መውደቅ ኦ እጅግ ይሻለኛል ምንም ቸር ብትሆን በአንተ አይዘበትም ጉዴን ለመሸፈን ምክንያት አላቀርብም ያው ከነበደሌ ራሴን ሰጥቻለሁ ምረህ ተቀበለኝ ቃልህን ጥሻለሁ አዝ፦ ስብራቴ የማይፈወስ ይመስላል መደኃኒቴ አንተ ግን ምን ይሳንሃል ምህረትህ ካለ ማጉረምረም ምን ይጠቅመኛል በእጅህ ውስጥ መውደቅ ኦ እጅግ ይሻለኛል ምንም እንኳን ዛሬ ሃፍረት ቢሸፍነኝ ፊትህን ለማየት ከቶ ቢያዳግተኝ በተስፋ ዝም ብዬ ቀኔን ጠብቃለሁ ድል ልታድሰኝ እንደምትችል አምናለሁ አዝ፦ ስብራቴ የማይፈወስ ይመስላል መደኃኒቴ አንተ ግን ምን ይሳንሃል ምህረትህ ካለ ማጉረምረም ምን ይጠቅመኛል በእጅህ ውስጥ መውደቅ ኦ እጅግ ይሻለኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection