አብን በዙፋኑ ወልድን በስተቀኙ በምድር የተገፋውን በክብር ሊገናኙ ፍሬ አፍርቶ ታይቶት ክርስቲያን በቃሉ ተፈፀመ ብሎ ወጣ ከሃሩሩ አዝ፦ ለረጅም ዘመናት ተቸግሮ ማቆም ክርስቲያን ተሻገረ ወላፈኑን ዘልቆ እውር ፈሪሳውያን በምናቸው ይዩ ብርሃን መፈንጠቁን ከችግር ይዩ በመከራ ናዳ በሰዎች ጫጫታ ሩጫውን አከተመ ጀግናው ሳይረታ አዝ፦ ለረጅም ዘመናት ተቸግሮ ማቆም ክርስቲያን ተሻገረ ወላፈኑን ዘልቆ ሃገር ሃገር ሲዞር ሲንከራተት ከርሞ መልኩ ተቀይሮ በመከራ ከስሞ ከጅራፍ ከዱላ ከጨካኞች ጡጫ ክርስቲያን አንቀላፋ አረፈ ከእርግጫ አዝ፦ ለረጅም ዘመናት ተቸግሮ ማቆም ክርስቲያን ተሻገረ ወላፈኑን ዘልቆ እንደነ ያዕቆብ በደም ተበክለን ለወንጌል ሊደፉ ለቃልኪዳናቸው በሰልፍ ቆመዋል ተራ ይጠብቃሉ ኢየሱስ (3x) ይላሉ አዝ፦ ለረጅም ዘመናት ተቸግሮ ማቆም ክርስቲያን ተሻገረ ወላፈኑን ዘልቆ