አዝ፦ ልብህ ጽኑ ይሁን አይላላ ጠንክር በአመንክበት ጌታ በፍፁም አትፈር (2x) ተድላና ደስታ መጽናናት በረከት ሁሌ መንደላቀቅ በተሟላ ሕይወት እንደዚህ አይደለም እንዲህ አትመልከት ክርስትና አንዳንዴ መከራም አለበት አዝ፦ ልብህ ጽኑ ይሁን አይላላ ጠንክር በአመንክበት ጌታ በፍፁም አትፈር (2x) የጨለማው ስልጣን ጥላውን ዘርግቶ ጠላት ኃይሉን ሲያሳይ እጅግ ተቆጥቶ በበትር ሲመጣ በቁጣ ሲያጠቃ ከመስቀሉ ወንድሜ አይጥፋ አዝ፦ ልብህ ጽኑ ይሁን አይላላ ጠንክር በአመንክበት ጌታ በፍፁም አትፈር (2x) ማምለጫ ስታሻ ቀዳዳ ስትፈልግ ጭላንጭል ውስጥ እንኳን ሲደፈን ሲመረግ በወህኒ ተጥለህ ሰው ሁሉ ሲረሳህ የሕይወትህ ጌታ የሚረሳህ አይምሰልህ አዝ፦ ልብህ ጽኑ ይሁን አይላላ ጠንክር በአመንክበት ጌታ በፍፁም አትፈር (2x) በምስራቹ ቃል በወንጌል ተሟገት ልብህ ሰፊ ይሁን አርቀህ ተመልከት ለማያልፈው እርስት ለአገርህ ተዋግተህ በላይ እንገናኝ ዘመንህን አጥለቅልቀህ አዝ፦ ልብህ ጽኑ ይሁን አይላላ ጠንክር በአመንክበት ጌታ በፍፁም አትፈር (2x)