Song Lyrics

ኢየሱስን ለብሰህ

Pastor Tesfaye Gabisso
Chrsitian Teshagere
የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቷል በጠላት ተከበሃል ክርስቲያን ተጠንቀቅ ዙሪያህን አስተውል ጉልበትህ አይላላ ጠንክረህ ተዋጋ ብድራትን አይተህ ያለልህን ኋላ አዝ፦ ኢየሱስን ለብሰህ የጦር ዕቃህን አንስተህ በእርሱ መልካም ጦርነት ተዋጋ ኢየሱስ ያሸንፋል ለድሉ አትስጋ በጦርነት ላይ መቁሰልም አለ ሞትም ቢሆን ጥቅም ነው ለጨለማው ገዢ እጅህን አትስጠው እስከ ሞትህ ታመን ነፍስህን አታክብራት ለታመነው ፈጣሪ አሳልፈህ ስጣት አዝ፦ ኢየሱስን ለብሰህ የጦር ዕቃህን አንስተህ በእርሱ መልካም ጦርነት ተዋጋ ኢየሱስ ያሸንፋል ለድሉ አትስጋ ባለጋራህ ዲያብሎስ ሊውጥህ እያገሳብህ ነውና በድምፁ አትፍራ አባትህ አለና መንጋጋውን ዘግቶ ከአፍ ያስጥልሃል ከቶም እንደማይጥልህ በግልጽ ያሳይሃል አዝ፦ ኢየሱስን ለብሰህ የጦር ዕቃህን አንስተህ በእርሱ መልካም ጦርነት ተዋጋ ኢየሱስ ያሸንፋል ለድሉ አትስጋ የውጊያው ጊዜ አሁን ነው ወንድም ተነስ ተጋጠመው ድል ትነሳለህ በርትተህ ታገለው የአብርሃም አምላክ ጋሻ ይሆንሃል ለአገርህም አብቅቶ አክሊል ይሰጥሃል አዝ፦ ኢየሱስን ለብሰህ የጦር ዕቃህን አንስተህ በእርሱ መልካም ጦርነት ተዋጋ ኢየሱስ ያሸንፋል ለድሉ አትስጋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection