Song Lyrics

አንተን አንተን ብዬ

Pastor Tesfaye Gabisso
Chrsitian Teshagere
አዝ፦ አንተን አንተን ብዬ እኔን ወደ ኋላ ጥዬ በእምነት እሻገራለሁ በድል ፊትህን አያለሁ ከቀደሙት ተምሬያለሁ የአንተን ተስፋ ጠብቃለሁ በእምነትህ ተመልከተኝ እምነትንም ጨምርልኝ አዝ፦ አንተን አንተን ብዬ እኔን ወደ ኋላ ጥዬ በእምነት እሻገራለሁ በድል ፊትህን አያለሁ የፍየልን ሌጦ ለብሰው መቅደስህን ተንተርሰው እየተንከራተቱ ብዙ አሉ ክብራቸውን ለአንተ የጣሉ አዝ፦ አንተን አንተን ብዬ እኔን ወደ ኋላ ጥዬ በእምነት እሻገራለሁ በድል ፊትህን አያለሁ በእምነት ሥምህን ጠሩ በፀሎት ለአንተ ነገሩ በላይ ሆነህ ሰማሃቸው ቃላቸውን አደመጥካቸው አዝ፦ አንተን አንተን ብዬ እኔን ወደ ኋላ ጥዬ በእምነት እሻገራለሁ በድል ፊትህን አያለሁ በእምነት ባሕርን ከፈቱ ከጠላት እጅ አመለጡ እነርሱን ልመስል እሻለሁ በእምነት ሥምህን ጠራለሁ አዝ፦ አንተን አንተን ብዬ እኔን ወደ ኋላ ጥዬ በእምነት እሻገራለሁ በድል ፊትህን አያለሁ በመንፈስ መልክትን ሰሙ ጌታ አንተን ተሳለሙ እምነትን ስጠኝ እራስህ እኔም አንተን ለምናለሁ አዝ፦ አንተን አንተን ብዬ እኔን ወደ ኋላ ጥዬ በእምነት እሻገራለሁ በድል ፊትህን አያለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection