አዝ፦ እስከዛሬ የጠበከን ከፍላጻ የሸፈንከን ዳርቻችንንም ያሰፋህልን እንባችንን ና አብስልን በማይገለጸው ክብርህ በማይካድ ጉልበትህ አንድነትን አሳየን ለእኛም ከለላ የሆንህ አዝ፦ እስከዛሬ የጠበከን ከፍላጻ የሸፈንከን ዳርቻችንንም ያሰፋህልን እንባችንን ና አብስልን የጠላትን ቁጣ አይተን ልካችንን ስንመስል ተስፋ ቆርጠን ወየው ስንል አማኑኤል ደረስክልን አዝ፦ እስከዛሬ የጠበከን ከፍላጻ የሸፈንከን ዳርቻችንንም ያሰፋህልን እንባችንን ና አብስልን በማባበል ሊያስማማን ካልተሳካው ሊያስፈራራን ጠላት ሲዝት ሲያሽካካብን ሴራውን ያከሸፍክልን አዝ፦ እስከዛሬ የጠበከን ከፍላጻ የሸፈንከን ዳርቻችንንም ያሰፋህልን እንባችንን ና አብስልን ድብልቅ ኑሮ ያልኖረ ከእግዚአብሔርም የተማረ ቢማቅቅም ያሸንፋል የአምላኩንም ሥም ያስጠራል አዝ፦ እስከዛሬ የጠበከን ከፍላጻ የሸፈንከን ዳርቻችንንም ያሰፋህልን እንባችንን ና አብስልን