አዝ፦ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ ድል ይገኛል ከጌታ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ መልስ ይመጣል ከጌታ የበረታ ሰልፍ ሲከበኝ ከኋላ ከፊት ቆይቼ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለልኝ ሊያዳምጠኝ እንባዬን በእጁ ጠርጐ ቃሉን ሰጥቶ አፅናናኝ አዝ፦ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ ድል ይገኛል ከጌታ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ መልስ ይመጣል ከጌታ ነፍስህ ብትራቆት ፍፁም ባዶ ስትሆን ያለህን አራግፈህ ዘርተህስታይ ራስህን ያሳለፍካቸውን ድሎች አስብ ተስፋህ ይለምልም ተንበርክከህ ብትቆይ ደግሞ መዳሰስህ አይቀርም አዝ፦ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ ድል ይገኛል ከጌታ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ መልስ ይመጣል ከጌታ ከድካም የበረቱ ሰዎች በድል ያለፉ ከኢየሱስ በስተቀኝ በላይ የተሰለፉ መንግሥታትን ድል ነስተው ያንን ምሽግ የናዱ የፀሎት ሰዎች ናቸው ጠላት ያርበደበዱ አዝ፦ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ ድል ይገኛል ከጌታ በትዕግሥት ፀጥታ በፀሎት ቆይታ መልስ ይመጣል ከጌታ