በእምነት መኖሪያዬን ሰርተህ ውብ አድርገህ ምግቤን ያለ ድካም እንድበላ ብለህ ያስቀመጥክኝን ሰው ወረት ሲደልለኝ ከሕይወት ሲያራቁተኝ በቸልታ አትየኝ አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ቦታ ፀንቼ እንድቆይህ መጥተህ ስትጐበኘኝ በእኔ ደስ እንዲልህ ፀጋህን አብዛልኝ ጌታ ሆይ እባክህ ልቤ እየቸኮለ እግሬ ሮጥ እያለ ውርደትን ለማየት ዓይኔ እየከጀለ ድንበር እየጣሰ ከኃጢአት እየዋለ የማታ የማታም ሚዛኔ ቀለለ አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ቦታ ፀንቼ እንድቆይህ መጥተህ ስትጐበኘኝ በእኔ ደስ እንዲልህ ፀጋህን አብዛልኝ ጌታ ሆይ እባክህ የጭንጫ ቡቃያ ፈጥኖ እየበቀለ ፀሐይ ስትወጣ ነዶ የተቃጠለ አስተምሮኛል እኔን ፍሬ እንዳፈራ አንስተህ አትጣለኝ የእኔ ጌታ አደራ አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ቦታ ፀንቼ እንድቆይህ መጥተህ ስትጐበኘኝ በእኔ ደስ እንዲልህ ፀጋህን አብዛልኝ ጌታ ሆይ እባክህ ቸኮል ያለ ሳዖል በዓይኖችህ ተንቆ ብላቴናው ዳዊት ተቀብቷል ልቆ ዓይኔን ግለጠውና ስፍራዬ ልወቀው አሳድገኝ እንጂ ዕድሜዬን አትቁረጠው አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ቦታ ፀንቼ እንድቆይህ መጥተህ ስትጐበኘኝ በእኔ ደስ እንዲልህ ፀጋህን አብዛልኝ ጌታ ሆይ እባክህ