Song Lyrics

አዎን ይሆናል

በጌተ ሰማኒ ጌታ ኢየሱስ ቃቶ በቀራንዮ ላይ ከጠላት ተዋግቶ በጐቹን አድኗል ነፍሱን ለሞት ሰጥቶ እንዲህ ያለ ፍቅር ከየት ይገኛል ከቶ (3x) መልካም እረኛ ስለ በጐቹ ነፍሱን ያኖራል በእርሱ የሚገባ በእርሱም የሚሰማራ ለዘለዓለም ይድናል ዘለዓለም ይኖራል መንጋውን ሊበትን እረኛውን መቶ ሰይጣን ቢጣጣርም እጅግ ተበራቶ ምርኮውንም መልሷል ኢየሱስ ድል ነስቶ ዛሬም ይደግመዋል ሕዝቦቹን ጐብኝቶ (3x) አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (2x) ሃዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል ዓለም የሌላትን መድህን አግኝተናል ስለዚህም እኛ ምንም ብንገፋ ማንም አይጥለንም ከዚህ ፅኑ ተስፋ (3x) አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (2x) በቅርብ በሩቅ የተበተናችሁ ጌታ ቅርብ ነውና ፍፁም አይግፋችሁ የእርሱን በጐነት ለዓለም ተናግራችሁ ለጽዮን ስብሰባ በእግዚአብሔር ያብቃችሁ (3x) ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ቶሎ ና ናና ሰብስበን ከተበታተንበት ወደ ውድ አገራችን ጥራን አከማቸን (2x) አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል እንጠብቃለም ለቅሷችንን በደስታ ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (2x) አዎን ይሆናል (አዎን ይሆናል) መቼ ይቀራል (መቼ ይቀራል) እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection