የዓለም ፍጻሜ ምልክቶች የጌታችን ቃሎች ትንቢቶቹ ተፈፅመዋል የሚበዙቱ የምሥራቹ ቀርቧል ሰዓቱ አዝ፦ ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ግርማ በድንገት ይመጣል በሰማይ ደመና ከቅዱሳኑ ጋር በክብር ይገለጣል ፊቱ ልትቆም ምን ያህል (2x) ተዘጋጅተሃል ረሃብ ቸነፈሩ የምድር መናወጥ የአህዛብ ዕውቀት መከራና ምጥ ፍጥረቱን ይዞ ሲያንገዳግደው የጨለማው ገዥ ጨንቆ ሲያብሰው አዝ፦ ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ግርማ በድንገት ይመጣል በሰማይ ደመና ከቅዱሳኑ ጋር በክብር ይገለጣል ፊቱ ልትቆም ምን ያህል (2x) ተዘጋጅተሃል ሃሰት አሰራር ተዓምራቱ የዓለም ሕዝቦችም ሲሳሳቱ ዋጋ ሲያስከፍል ጌታን መጥራቱ ቀኑም ቅርብ ነው የድል ንጋቱ አዝ፦ ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ግርማ በድንገት ይመጣል በሰማይ ደመና ከቅዱሳኑ ጋር በክብር ይገለጣል ፊቱ ልትቆም ምን ያህል (2x) ተዘጋጅተሃል ፍፁም ባላሰብከው ሰዓት ይመጣል ነቅቶ መጠበቁ ይሻልሃል በምቾት ወጥመድ እንዳትታለል በጸሎት እየተጋህ ተጠንቀቅ አዝ፦ ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ግርማ በድንገት ይመጣል በሰማይ ደመና ከቅዱሳኑ ጋር በክብር ይገለጣል ፊቱ ልትቆም ምን ያህል (2x) ተዘጋጅተሃል ወንጌል ታውጆ የዘለዓለም ሰዎች አምልጠው ከጥፋት ዓለም የተባረከ ተስፋችን ኢየሱስ ክፉን ደምስሶ በድል ሊነግስ አዝ፦ ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ግርማ በድንገት ይመጣል በሰማይ ደመና ከቅዱሳኑ ጋር በክብር ይገለጣል ፊቱ ልትቆም ምን ያህል (2x) ተዘጋጅተሃል