(1)ጌታን ሲጠብቅ ታምኖ የኖረ ብርሃንን ሳያይ ማነው የቀረ የነፍስህ ጥማት ናፍቆትህ ሁሉ ፀንተህ ብትቆይ መልስ ያገኛሉ አዝ፦ የጉስቁልና ዘመን ያልፍና ችግር ስቃይ ይታሰብና ጌታ ዳግመኛ ይጐበኝሃል አዲስ ሰው አርጐ ይለውጥሃል (2x) (2)ተረስቻለሁ ተጥያለሁኝ ለምንም ነገር የማልጠቅም ነኝ ለምን ትላለህ ጌታ ያስብሃል በራሱም ጊዜ ከፍ ያደርግሃል አዝ፦ የጉስቁልና ዘመን ያልፍና ችግር ስቃይ ይታሰብና ጌታ ዳግመኛ ይጐበኝሃል አዲስ ሰው አርጐ ይለውጥሃል (2x) (3)የኤልያስ አምላክ ወዴት ልበልህ በፍፁም ነፍስህ ተግተህ ፈልገው ከቶ የማይደክም የማይታክተው የአባትህ አምላክ ጌታ ቅርብ ነው አዝ፦ የጉስቁልና ዘመን ያልፍና ችግር ስቃይ ይታሰብና ጌታ ዳግመኛ ይጐበኝሃል አዲስ ሰው አርጐ ይለውጥሃል (2x)