አዝ፦ በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ ስለ ሕይወት ቃል ፀንቶ ተዋድቆ በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ በጎ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞተ የሸለቆ ሌት በተጨነቀ ልቡ እረፍት አግኝቶ ጉዞውን ቢጀምር ወደ ሰማያዊ አገር አግኝቶ ሰይጣን በተንኮል በወጥመዱ አጥሮ መንገድ ቢዘጋበት ጌታም ይህን አይቶ ወጥመዱን ሰባብሮ በሩን ከፈተልን አዝ፦ በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ ስለ ሕይወት ቃል ፀንቶ ተዋድቆ በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ በጐ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞተ የሸለቆ መዋጋትን እንዲለምድ ሸለቆ ወርዶ ከቤት ከንብረቱ ከነፍሱ አምልጦ ጌታውን ወዶ ሰልፉ በረታና ክፉኛ ተጠግቶ እጅና እግሩ ዝሎ ኢየሱስ ደርሶለት ድልን አወጀለት ባላንጣውን ጥሎ አዝ፦ በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ ስለ ሕይወት ቃል ፀንቶ ተዋድቆ በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ በጐ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞተ የሸለቆ እጆቹን በእርፉ ላይ አንዴ አሳርፏል ወደኋላ ማየት ነውር በመሆኑ ሥራውን ቀጥሏል እምነት ሳይጓደል አደራ ሳይበላሽ ተጠንቆ ታግሎ እፎይ ማለቱ ነው በክብር ተራራ አክሊል ተቀብሎ አዝ፦ በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ ስለ ሕይወት ቃል ፀንቶ ተዋድቆ በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ በጐ ወታደር . በድል አለፈ ያንን የሞተ የሸለቆ (2x)