Song Lyrics

እውነተኛ ዳኛ

የክሱን ክምችት የዕዳውን ስፋት ደምስሰህልናል በመስቀልህ ምህረት አንተ አጽድቀኸናል ማነው የሚከሰን ከጸናችውን እጅህ የለም የሚነጥቀን ጌታ ሆይ ተመሥገን አዝ፦ አንተ የእውነት አምላክ እውነተኛው ዳኛ ከከሳሽ ያዳንከን ፈርደህልን ለእኛ ጌታ ከመንበርህ ከሥር ከዙፋንህ መድኃኒትህን ልቀቅ በአንተ አርፏል ሕዝብህ ተረታሁኝ ብሎ ጠላትም ባይተኛ የማንተቀላፋ ጌታ አለህ ለእኛ ደምፅህን ሲሰማ አጥማጅህ ገለል ይላል ከመከራም ስጋት በአንተ ያመነ ያርፋል ተከልሎ ይኖራል አዝ፦ አንተ የእውነት አምላክ እውነተኛው ዳኛ ከከሳሽ ያዳንከን ፈርደህልን ለእኛ ጌታ ከመንበርህ ከሥር ከዙፋንህ መድኃኒትህን ልቀቅ በአንተ አርፏል ሕዝብህ ከሳሻችን ወድቆ እኛ ተነስተናል ጉልበታችን ፀንቶ እነሆ ቆመናል ታዳጊያችን ሆይ ተመሥገን እንበልህ ከአዳኙ ወጥመድ የወጣን ሕዝበህ ማርኮናል ፍቅርህ አዝ፦ አንተ የእውነት አምላክ እውነተኛው ዳኛ ከከሳሽ ያዳንከን ፈርደህልን ለእኛ ጌታ ከመንበርህ ከሥር ከዙፋንህ መድኃኒትህን ልቀቅ በአንተ አርፏል ሕዝብህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection