ልከፍለው የማልችል ነበረብኝ ዕዳ ችግሬን ባዋየው ማን እኔን ሊረዳ ኃጥያተኛ ብሎኝ ሁሉም ተጸየፈኝ እንዲፈረድብኝ ጠላትም ከሰሰኝ (2x) ማነው የሚያድነኝ ከእንግዲህ ብዬ ብቻዬን ሳለቅስ አገኘኝ ጌታዬ ዕዳዬን ተወልኝ እንባዬን አበሰው የሕይወቴን ቁስል በቁስሉ ፈወሰው (2x) ብዙ ኃጥያቴ ተሰርዮልኛል አብዝቼ እንድወደው በእርግጥ ይገባኛል ዋጋው የከበረ የሽቶ መስዋዕት ከደስታ እንባ ጋር ምነው ባቀርብለት (2x) ለቅሶዬን ለደስታ እርሱ ከለወጠው ሽቶ ላፈስለት ብልቃጡን ብሰብረው ማነው ቅር የሚሰኝ ጌታዬን ባከብረው ሃብቴን ብቻ ሳይሆን ሕይወቴን ብሰጠው (2x) ማንም በውድቀቴ ያላዘነልኝን በምድር ላይ ፍፁም ተስፋ የሌለኝ ሞቴን ወደ ሕይወት መለሰው ኢየሱስ ስለፍቅርድ ብዛት ሥምህን ልቀድስ (2x) ማን እንዳንተ ጌታ ልብን ሊመረምር ማን ጠልቆ ሊረዳ የሰዎችን ችግር ዕውቀትህ የላቀ መሃሪዬ ነህ ምሥጋናና ክብር ይሁን ለሥምህ ይሁን ለሥምህ (2x) ይሁን ለሥምህ (2x)