በቀራንዮ መስቀል ላይ በደዌ የደቀቀው ነፍሱን ስለ ኃጥያቴ መስዋዕት ያደረገው የሞትን ቀንበር ሰብሮ እኔኑ ሊያወጣ ነው ማዳኑን ቀምሻለው ምን አለ የምመልሰው (2x) አዝ፦ ክብር ለኢየሱስ ይሁን አየን አሸናፊነቱን ኃያል እንደ እርሱ የለም ይንገሥ ለዘለዓለም (2x) የተናቀ ደካማ ቢመስልም አመጣጡ ከእሰይ ልጅ ከዳዊት ሥር የወጣው ቁጥቋጡ ኢየሱስ አሸነፈ ፍሬው ምድርን ሸፈነ የእግዚአብሔር ፈቃድ በእጁ ተከናወነ (2x) አዝ፦ ክብር ለኢየሱስ ይሁን አየን አሸናፊነቱን ኃያል እንደ እርሱ የለም ይንገሥ ለዘለዓለም (2x) በደሙ ኃይል ጸደቅን በሥሙ ድል አገኘን ማነው የሚቋቋመን ማንስ ነው የሚገታን እንገሰግሳለን አሸናፊውን ይዘን ወደ ቅድስቷ ሃገር በድል እንገባለን (2x) አዝ፦ ክብር ለኢየሱስ ይሁን አየን አሸናፊነቱን ኃያል እንደ እርሱ የለም ይንገሥ ለዘለዓለም (2x) ክብር ምሥጋና ይዘን ከፊቱ እንቀርባለን በዙፋኑ ላይ ላለ እንሰግድለታለን ሁሉን የረታ ጌታ ንገሥ እንለዋለን አቤት ለዘለዓለም እርሱ ኃያል ነው አሜን (2x) አዝ፦ ክብር ለኢየሱስ ይሁን አየን አሸናፊነቱን ኃያል እንደ እርሱ የለም ይንገሥ ለዘለዓለም (5x)