Song Lyrics

በእምነት ድል እየነሱ

Pastor Tesfaye Gabisso
Abetu Mebarekin Barken
አዝ፦ በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን የቀደሙትን እያየን ከፊታችን ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን የሕይወት ምርጫችን እርሱ ነውና ዋስትናችን (2x) ከሁሉ የሚበልጠውን ተመልክተው ከየምድሩ ጉድጓድ ተቅበዝብዘው ነፍስን ከሚዋጋ ምኞት ርቀው ወንዙን ተሻገሩ አሸንፈው (3x) አዝ፦ በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን የቀደሙትን እያየን ከፊታችን ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን የሕይወት ምርጫችን እርሱ ነውና ዋስትናችን (2x) ቅን ከምትመስል ሰፊ መንገድ ወጥተን በጠባቡ ስንሰደድ በዚህ ጐዳና ላይ ሕይወት አለ ቆርጦ ለሚከተል የታደለ (3x) አዝ፦ በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን የቀደሙትን እያየን ከፊታችን ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን የሕይወት ምርጫችን እርሱ ነውና ዋስትናችን (2x) ባለ ፀጋ ሲሆን ደህይቶልን ባለ ማዕረግ ሲሆን ተዋርዶልን እውነተኛውን ፍቅር ገለጸልን እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን (3x) አዝ፦ በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን የቀደሙትን እያየን ከፊታችን ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን የሕይወት ምርጫችን እርሱ ነውና ዋስትናችን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection