Song Lyrics

አቤቱ መባረክን ባርከን

Pastor Tesfaye Gabisso
Abetu Mebarekin Barken
አዝ፦ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ ያቤጽንም ሰምተሃል እንደዚህ ሲለምንህ ነፍሱን ባርከህለታል አገሩንም አስፍተህ አዝ፦ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ በልጅህ ስቃይና በጣር የተወለደን እኛም ፍሬዋችህ ነን አስባስበህ ጠብቀን አዝ፦ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ ከፊትህ አትጣለን እንማጸንሃለን በሞገስህ አስበን በምህረትህ ጐብኘን አዝ፦ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ ሰማያቱም ይከፈት መንፈስህ ያፍሰስልን ሕይወታችን ትረስርስ ነፍሳችን ትጥገብልን አዝ፦ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ ብቻችንን እንቅር አብዛን እየባረክህ አበልጽገን በፀጋህ ታደገን በቃልህ አዝ፦ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ እግዚአብሔርን በማወቅ ምድር እስክትሞላ ምልጃችን ይቀጥላል ጉልበታችን ሳይላላ አዝ፦ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection