Song Lyrics

እንደተቀበልኩት ምህረት

Pastor Tesfaye Gabisso
Abetu Mebarekin Barken
አዝ፦ እንደ ተቀብለኩት ምህረት እንደ ቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን አሳት እስራቴን ቆርጠህ ቀንበሬን ሰብረሃል ነፍሴ እንድታከብርህ ነጻ አውጥተኸኛል ባርነት አበቃ ልጄ ነህ ብለኸኛል በደምህ ቃልኪዳን የአንተ አድርገኸኛል አዝ፦ እንደ ተቀብለኩት ምህረት እንደ ቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን አሳት የተፍገመገመ ከውድቀት እንዲተርፍ የደከመን ሁሉ በቃልህ እንድደግፍ አንቃኝ በማለዳ ቀስቅሰኝ ከእንቅልፍ ታማኝ ሎሌ አድርገኝ ልብን የሚያሳርፍ አዝ፦ እንደ ተቀብለኩት ምህረት እንደ ቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን አሳት ስንፍናዬን አርቅ በተግሳፅህ በትር እንድተጋ እርዳኝ ከፀጋህ ዙፋን ሥር ኢየሱስ ያድናል ብዬ እንድመሰክር ሕይወቴን ሙላልኝ በመስቀልህ ፍቅር አዝ፦ እንደ ተቀብለኩት ምህረት እንደ ቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን አሳት ጥበብ ለሌላቸው ለማያስተውሉ ለተማሩም ሰዎች አውቀናል ለሚሉ ወንጌሉን ልናገር እንዲድኑ አምነው ለእነዚህ ሁሉ ዕዳዬ ትልቅ ነው አዝ፦ እንደ ተቀብለኩት ምህረት እንደ ቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን አሳት ወንጌል አይቆጠብ አይወሰን በክልል እስከ ምድር ዳር ይሂድ ቃልህ ሳይከለከል ለቅርቡ ለሩቁ ጽድቅህም ይታደል ኢየሱስን አግኝቶ ፍጥረት እሰይ ይበል አዝ፦ እንደ ተቀብለኩት ምህረት እንደ ቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን አሳት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection