Song Lyrics

አዲስ ዝማሬ እንዘምር

Pastor Tesfaye Gabisso
Abetu Mebarekin Barken
አዝ፦ አዲስ ዝማሬን እንዘምር ለመድኃኒታችን ክብር የምሥጋናችንን ሽታ እናሳርግ በዕልልታ (2x) በእረኛቸው የታመኑ በመስኩ የተሰማሩ ዱካውን እየተከተሉ ለደህንነት የተጠሩ ከጨካኝ አውሬ የዳኑ ከመታረድ የተረፉ ሃሴትን እንደሚያደርጉ በአጥፊው ጥፋት ስላልጠፉ አዝ፦ አዲስ ዝማሬን እንዘምር ለመድኃኒታችን ክብር የምሥጋናችንን ሽታ እናሳርግ በዕልልታ (2x) ማቃችንን ቀዷልና ፀጋውን አልብሶናልና ክብራችን ትዘምርለት ደርሶ አጽናንቶናልና ጉዳታችንን የሚሹ ጉድጓድ ምሰው የጠበቁን አጋንንት አፍረዋልና ያደፈጡት ሊያጠቁን አዝ፦ አዲስ ዝማሬን እንዘምር ለመድኃኒታችን ክብር የምሥጋናችንን ሽታ እናሳርግ በዕልልታ (2x) በፍፁም ልብ እንዘምር በአምላካችን ደስ ይበለን እናጨብጭብ ዕልል እንበል ለምንስ እንቆጥባለን በምሥጋናችን ዝማሬ ምሽጉን እናፈርሳለን በመንፈሳዊው ጦር ዕቃ ድል በድል እንሄዳለን አዝ፦ አዲስ ዝማሬን እንዘምር ለመድኃኒታችን ክብር የምሥጋናችንን ሽታ እናሳርግ በዕልልታ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection