Song Lyrics

ጠቢብ በጥበቡ አይመካ

Pastor Tesfaye Gabisso
Abetu Mebarekin Barken
አመጻዬ ወደ ምድረ በዳ ወሰደችኝ ውኃ በሌለው በረሃ አንከራተተችኝ ለውድቀቴ እውቀት ትዕቢትን አስተማረችኝ ጥማት ሲያቃጥለኝ እልህ ሲታገለኝ እውነት ስትወርሰኝ ጥበብ ስትገስጸኝ መንፈሱ ሲረታኝ ጌታን አገነሁት አዝ፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍርድን በምድር ላይ ማድረጉን ያወቀ በጌታ ይመካ (2x) ሰማያዊ ጥበብ ዓይንን ትከፍታለች ለሰነፎች ብልሃትን ታስተምራለች ከምዝምዝ ወርቅና ከቀይ ዕንቁ ትበልጣለች አጥብቀህ ብትሻት ብትፈላልጋት ድምጽህን አንስተህ ጥበብን ብጠራት ያን ጊዜ ታውቃለህ እግዚአብሔርን መፍራት አዝ፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍርድን በምድር ላይ ማድረጉን ያወቀ በጌታ ይመካ (2x) የዚህች ዓለም መርማሪ ወዴት አለ የዘመናትን ጥያቄ ያቃለለ ኢየሱስ ነው ሊቁ ለእኛ የተሰቀለ ከበረሃው መሃል ሕይወት ያፈለቀ የሰይጣንን ስልጣን መትቶ ያደቀቀ ለእርሱ ስንሸነፍ ጥያቄው አለቀ አዝ፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍርድን በምድር ላይ ማድረጉን ያወቀ በጌታ ይመካ (2x) አ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection