የሞትንስ ፍርድ ብዙ ጊዜ ሰምተናል በሕይወት ለመኖር ዕለት ዕለት ሞተናል የኢየሱስን ሞት ተሸክመን ዞረናል በዚህ ሁሉ ግን በምህረቱ ኖረናል አዝ፦ እጁን ዘርግቶ ጌታ ባይረዳን ከእኛ ጋር ሆኖ በችግራችን ባይታደገን እንደዚህ ፈጥኖ ረግረጉ ውጦን ልንጠፋ ነበር ውኃ አስጥሞን ዛሬ ግን ድነን በሕይወት አለን ኢየሱስ አውጥቶን በእምነት እንጂ በምናየው አይደለም ከጌታ በቀር እኛ ትምክህት የለንም ጽድቃችን እንኳን ለዚህ አላበቃንም ፀጋው አጽንቶን ክርሱ አልተለየንም አዝ፦ እጁን ዘርግቶ ጌታ ባይረዳን ከእኛ ጋር ሆኖ በችግራችን ባይታደገን እንደዚህ ፈጥኖ ረግረጉ ውጦን ልንጠፋ ነበር ውኃ አስጥሞን ዛሬ ግን ድነን በሕይወት አለን ኢየሱስ አውጥቶን ሕያዋን ሆነን በእርሱ እንኖራለን የጌታን ሥራ ዛሬም እንገልጻለን ክብር ለሥሙ ሞገስ ለሥሙ ብለን ያለንን ሁሉ ለእርሱ እንሰዋለን አዝ፦ እጁን ዘርግቶ ጌታ ባይረዳን ከእኛ ጋር ሆኖ በችግራችን ባይታደገን እንደዚህ ፈጥኖ ረግረጉ ውጦን ልንጠፋ ነበር ውኃ አስጥሞን ዛሬ ግን ድነን በሕይወት አለን ኢየሱስ አውጥቶን