እግዚአብሔርን ይሄ ነው ተስፋ ያደረኩት ታማኝነቱን አይቼ እጄን ልቤን የሰጠሁት ያለ አዋቂዎች ልቦና በሰዎች ተስፋ ያደርጋል ግን እግዚአብሔር ብቻ ድህንነትን ያዘጋጃል አዝ፦ እጅግ ተቸግሬ ስማፀን አይተኸኝ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ አትፍራ እያልከኝ በመጽናናት ሞልተህ ደስታን ታስታጥቀኛለህ የልቤ አምላክ ሆይ የዘለዓለም ዕድል ፈንታዬ ነህ የተማሰው ጉድጓድ አፉን በእኔ ላይ አልዘጋም ጉልበቴ ባለቀ ጊዜ ለብቻዬ አልተውከኝም ስለ ትንሿ እምነቴ ከባለጋራ ተሟግተህ የድል አምባ አስረገጥከኝ ውጊያውን ሁሉ ፈጽመህ አዝ፦ እጅግ ተቸግሬ ስማፀን አይተኸኝ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ አትፍራ እያልከኝ በመጽናናት ሞልተህ ደስታን ታስታጥቀኛለህ የልቤ አምላክ ሆይ የዘለዓለም ዕድል ፈንታዬ ነህ ምሥጋናዬን እያዜምኩኝ በአንተ ደስ ይለኛል በከንቱ በሚጠሉኝ ፊት ሞገስ አጐናጽፈኸኛል ዓለም ብትሰርዘኝም የሕይወት መዝገብ አውቆኛል እስከ መጨረሻው ድረስ ሕይወቴ በአንተ ይጸናል አዝ፦ እጅግ ተቸግሬ ስማፀን አይተኸኝ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ አትፍራ እያልከኝ በመጽናናት ሞልተህ ደስታን ታስታጥቀኛለህ የልቤ አምላክ ሆይ የዘለዓለም ዕድል ፈንታዬ ነህ