ሕዝብህ ይጠብቅሃል ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! መገለጥህ ናፍቆታል ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! እባክህ ናልኝ ሳትቆይ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! ጊዜው አልደረሰም ወይ ? ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! አዝ፦ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! (3x) ጊዜው አልደረሰም ወይ? ስምህን ስለወደደች ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! ነፍሴ ስድብን ጠገበችና ጌታዬ ጌታዬ ሆይ! ባርኮቷን እያሰበችና ጌታዬ ጌታ ሆይ! ዛሬም በአንተ ታምናለችና ጌታዬ ጌታ ሆይ! አዝ፦ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! (3x) ጊዜው አልደረሰም ወይ? ድካሙ ሳይበረታ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! አርበኛው ሳይረታና ጌታዬ ጌታ ሆይ! የተጋዳይ አለኝታ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! በጠላትህ ላይ በርታ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! አዝ፦ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! (3x) ጊዜው አልደረሰም ወይ? ጣኦቱ ተሰባብሮ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! ልመልከት ስምህ ከብሮ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! ከጥንት እንደታወቅህ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! ምድር አንተን ትወቅ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! አዝ፦ ና ጌታዬ ጌታ ሆይ! (3x) ጊዜው አልደረሰም ወይ?