በደልን ይቅር የሚል አመጻን የሚያሳልፍ ከጥፋት ሊያድናቸው በሕዝቡ ላይየሚሰፍፍ እንዳንተ ያለ አምላክ ማነው ምህረቱ የበዛ? ቅዱሳንህ ሲሰደዱ መከራውም ሲበዛ አዝ፦ ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ የተቀደሰ መቅደስህን በጠላት አታስረግጥ የእግዚአብሔር ዕድል ፈንታበዙፋኑ እኮ ነው ! ሊያመልከው ሊያገለግለው ከግብጽ አገር ያፈለሰው አርነቱን በባርነት ሊተካ የሚከጅለው ይገባኛል የሚል ማነው ? ሕዝቡ የእግዚአብሔር ነው! አዝ፦ ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ የተቀደሰ መቅደስህን በጠላት አታስረግጥ እስከዛሬከብረሃል በአህዛብ ተፈርተሃል የጠላትን እርግማን በረከት አድርገሃል የአሳዳጁን ፈረሶች በባሕር አስጥመሃል በክንድህ ተከላክለህ ርስትህን ጠብቀሃል አዝ፦ ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ የተቀደሰ መቅደስህን በጠላት አታስረግጥ (2x)