Song Lyrics

ከንስሃ ወዲያ

Pastor Tesfaye Gabisso
Abetu Mebarekin Barken
የጠላትህን ክስ ሊደመስስልህ ከዓብ ዘንድ የቆመ ጠበቃ አለልህ የኃጢአትህን ሸክም ተናዘህ እረፈው በደሙ ያጥበዋል ለኢየሱስ ንገረው አዝ፦ ደስ ይበልህ ወንድሜ ከሳሽህ ተጥሏል የኃጢአትህ ዋጋ በጌታ ተከፍሏል ምህረቱን ተቀበል ኃዘንህን እርሳው ከንስሐ ወዲያ ልብህን ደስታ ይሙላው በእድፋሙ ልብስህ ሰውነትህ ተከድኖ በአፍረት ተውጠህ በደልህ ተጋኖ ምንም ነገር ቢሆን ከቶ ተስፋ አልቆርጥም ብለህ ተሟገተው ከፀጋው አልሸሽም አዝ፦ ደስ ይበልህ ወንድሜ ከሳሽህ ተጥሏል የኃጢአትህ ዋጋ በጌታ ተከፍሏል ምህረቱን ተቀበል ኃዘንህን እርሳው ከንስሐ ወዲያ ልብህን ደስታ ይሙላው ጠላትህን ጥሎ እስራትህን ቆርጦ ክስህን ደምስሶ ፍርድህን ለውጦ ያ የፍቅር አምላክ ምህረትን አውጇል ልብስህም እንዲቀየር ትዕዛዝን አውጥቷል አዝ፦ ደስ ይበልህ ወንድሜ ከሳሽህ ተጥሏል የሃጥያትህ ዋጋ በጌታ ተከፍሏል ምህረትን ተቀበል ሃዘንህን እርሳ ከንስሃ ወዲያ ልብህን ደስታ ይሙላው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection