አዝ፦ የአምላኩ ፈቃድ ፈቃዱ ሆኖ በፍጹም ነፍሱ በጌታ ታምኖ በነገር ሁሉ ሕይወቱ ረክቶ ጻድቅ ይኖራል በቃሉ ጸንቶ (2x) የሥጋ ምኞት የዓይንም አምሮት የዓለም ፍቅር ልቡን አታልሎት በጌታ መሆን ሞኝነት መስሎት ክርስትናዉን አውልቆ ጥሎት ያንን ሰው እዩት ሲሮጥ ወደሞት አዝ፦ የአምላኩ ፈቃድ ፈቃዱ ሆኖ በፍጹም ነፍሱ በጌታ ታምኖ በነገር ሁሉ ሕይወቱ ረክቶ ጻድቅ ይኖራል በቃሉ ጸንቶ (2x) የጌታን ፈቃድ ቀድሞ እየሮጠ በምኞት ባሕር ገብቶ ተዋጠ ዝናን ፍለጋ ሄደ ዋተተ እርካታን ጥሎ እየከነፈ እንደተጠማ ሳይረካ ሞተ አዝ፦ የአምላኩ ፈቃድ ፈቃዱ ሆኖ በፍጹም ነፍሱ በጌታ ታምኖ በነገር ሁሉ ሕይወቱ ረክቶ ጻዲቅ ይኖራል በቃሉ ጸንቶ (2x) እንግዳው ሰው ሆይ ! የምድረበዳው የማይረባህን የምትመኘው ማንነትህን የዘነጋኸው ምኞት ኃጢአትን ኃጢአት ሞትን እንደምትወልድ እንዴት አጣኸው? አዝ፦ የአምላኩ ፈቃድ ፈቃዱ ሆኖ በፍጹም ነፍሱ በጌታ ታምኖ በነገር ሁሉ ሕይወቱ ረክቶ ጻድቅ ይኖራል በቃሉ ጸንቶ (2x) የሥጋ ሩጫ ከእንግዲህ በቅቶ ከንቱ መባከን ከእንግዲህ ቀርቶ አርፈህ ተገዛ ፈቃዱን አውቀህ የጌታን ምክር ቃሎቹን ንቀህ እንዳትቀጣ ዳግም አምጸህ አዝ፦ የአምላኩ ፈቃድ ፈቃዱ ሆኖ በፍጹም ነፍሱ በጌታ ታምኖ በነገር ሁሉ ሕይወቱ ረክቶ ጻድቅ ይኖራል በቃሉ ጸንቶ (2x)