የልቤን ስፈጽም አምላኬን ሳልፈራ ለኋለኛው ዘመን ሳከማች መከራ ኃጢአትን ስዘራ የኖርኩትን ኑሮ ፀጋህ አሳመረው ሕይወቴን ቀይሮ (2x) አዝ፦ እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግአስተምረኝ (2x) ፈቃድህን አውቆ መታዘዙ ጠቅሞኝ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ሆኖልኝ መልካም ሥርዓትህን ተምሬ ተምሬ በእንግድነት ሐገር እዘምራለሁ ዛሬ አዝ፦ እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግአስተምረኝ (2x) ፈቃድህ ድንቅ ነው የፈጸምከው በእኔ ለዛሬም ለነገም ባንተ ላይ ነው ዓይኔ በምሄድበትም መንገዴን አሳየኝ በቀረልኝ ዘመን ፈቃድህን አስታውቀኝ (2x) አዝ፦ እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግአስተምረኝ (2x)