Song Lyrics

ጌታዬ አምላኬ

Pastor Tesfaye Gabisso
Abetu Mebarekin Barken
ማሰሮው ሲሰበር ድብቁ ብርሃን ይወጣል ስንዴው ሲበሰብስ ቡቃያው ብዙ ያፈራል ጌታዬ አምላኬ የተሰበረ ልብ ያሻኛል ድምፅህን እንድሰማ የተግሳጽ ይሁን ወይም የምክር በድንግዝግዝ ጊዜ ወድቄ እንዳልሰበር ጌታዬ አምላኬ የተከፈተ ጆሮ ያሻኛል አንተን ለመመልከት ሁልጊዜ በፊቴ ስትሄድ ወደ ቀጠሮአችን ቦታ በብርሃንህ እንድራመድ ጌታዬ አምላኬ ጤንነት ያለው ዓይን ያሻኛል ሰላምን ለማውራት የምሥራች ይዤ እንድሮጥ ፅድቅን ለተጠሙ ምንጩን እነሆ ለማለት ጌታዬ አምላኬ የሚራመዱ እግሮች ያሹኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection