Song Lyrics

አንተ ግን

Pastor Mesfin Mamo
Special Edition
ሁኔታውን ስናይ እየሆነ ያለውን ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ሚመስለውን ለምን ይኼ ሁሉ እግዚአብሔር ካለህ ስትል ነፍስ ስትቃትት ኸረ ያምላክ ያለህ አንተ ግን በዙፋንህ ተረጋግተህ ተቀምጠሃል ሁሉንም አውቀህ እግዚአብሔር ከጅማሬ እስከፍጻሜው ባለቤት ነህ የታሪክ ጸሐፊው ባንተ ማረፍ ነው መልካሙ ምርጫ ሌላ እኮ የለም ከቶ ያለው ብልጫ ኑሮ ሲወሳሰብ ሰዉ ግራ ገብቶት ነገ አልታይ ብሎት ውሉ ሲጠፋበት እግዚአብሔር እያለ ለምን ይኼ ሆነ እያለ የሰው ልጅ እንቅልፍ ካይኑ ሸሸ አንተ ግን በዙፋንህ ተረጋግተህ ተቀምጠሃል ሁሉንም አውቀህ እግዚአብሔር ከጅማሬ እስከፍጻሜው ባለቤት ነህ የታሪክ ጸሐፊው ባንተ ማረፍ ነው መልካሙ ምርጫ ሌላ እኮ የለም ከቶ ያለው ብልጫ ሁሉ እኮ በእጅህ ነው አሳብህ ጥልቅ ነው ላመኑብህ መታመኛ እግዚአብሔር ነህ መዳኛ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection