Song Lyrics

ጌታን ልባርከው

Pastor Mesfin Mamo
Shilimate Neh
ኑሮ ብዬ እኔ የያዝኩት ሕይወት ብዬ የመረጥኩት የሚተካ ያልተገኘለት ኢየሱስ ነው የሰጠኝ እረፍት (2x) አዝ፦ ከእርሱ ሌላም አልፈልግም ሌላውም አልሞተልኝም ያለኝን ሁሉ ብሰጠው አይቆጨኝ ለእርሱ ባፈሰው እስቲ ልባርከው እስቲ ልባርከው (4x) አለኝ ብዬ የምኮራበት በታች አለው እኔን የሚያስንቅ በብር በወርቅ የማይለወጥ ኢየሱስ ነው ሰላም የሚሰጥ (2x) አዝ፦ ልቤ ሚሻው የተጠማው የማወጣው የማወርደው መገኘቱ የሚናፍቀው ሌላ አይደለም ኢየሱስ ነው እስቲ ልባርከው እስቲ ልባርከው (4x) ከአምላኬ ጋር ውዬ ባድር የሚመረር. (1) . አንዳች ነገር ሌላ የለም ከእርሱ በቀር ሕይወቴ ነው ጌታ እግዚአብሔር ጌታ እግዚአብሔር (2x) ጌታን ልባርከው ጌታን ልባርከው (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection