ክብር ያስመለሱ መሰውያን ያደሱ ሁሉም የረሱትን በእድሜያቸው ይነሱ እግዚአብሔርን ሽተው ታሪክ ያስለወጡ በየዘመናቸው ለእውነት የተሰጡ ነበሩ አምላካቸውን ፈገግ ያስደረጉ ከእጁ ይልቅ ፊቱን ለልብ/ከምር የፈለጉ (2x) በዘመኔ ሁሉ እኔም ሌላ አልሻም አንተን እንጂ ጌታ ሌላ አላሳድድም በልቤም ዙፋን ላይ ሌላ አይቀመጥም ለአንተ እንጂ አምላኬ ለማንም አይሆንም ብዙዎች ረክተዋል የእጅህን ስራ አይተው እንጀራም ተርበው ስላበላሃቸው በከንቱ ፈለጉህ ደግመህ እንድጸጣቸው በቃኝ በማያውቀው ከንቱ መሻታቸው እኔ ግን አንዲት ነገር እለምንሃለሁ ከምትሰጠኝ በላይ አንተኑ እሻለሁ (2x) ወደቀኝም ሳልል ወደግራም ሳላይ የመደበልኝን ተቀብዬ ከላይ ሩጫዬን እሮጣለሁ እርሱ እየመራኝ በመጨረሻው ቀን በእጣ ክፍሌ እንድገኝ ወሰንኩኝ ላልመለስ እስከመጨረሻ ከአምላኬ በስተቀር ልቤም ሌላ አይሻ (4x)