ያበጃጁኝ እጆችህ እንዴት የተዋቡ ናቸው የደሙትም እጆችህ እኔንም ያቀፉ ናቸው ዛሬም መጥተህ በእኔ ላይ ጌታዬ ሆይ ጫናቸው (2x) የማይጠገብ ነው የአንተ መገኘት እንደ ወንዝ የሚፈስ አለበት በእርግጥ (2x) አዝ፦ አሜን አሜን ብዬ ለአንተ እሰግዳለሁ ላከበርከኝ ጌታ ምን እላለሁ አሜን አሜን አሜን ብዬ ለአንተ እሰግዳለሁ ላከበርከኝ ጌታ ምን እላለሁ አንተ ከነካኸኝ ምን ይቀርብኛል ክብርህ ይህን ልቤን ፈጽሞ ያጠግባል (2x) አዝ፦ አሜን አሜን ብዬ ለአንተ እገዛለሁ ለወደድከኝ ጌታ ምን እላለሁ አሜን አሜን አሜን ብዬ ለአንተ እገዛለሁ ለወደድከኝ ጌታ ምን እላለሁ አንተ ስትጭንብኝ ሙሉ ሰው እሆናለሁ እስራቴ ሁሉ ጠፍቶ አገኛለሁ በነካኸኝ ጊዜ ጉልበቶቼ ጸኑ በረታሁ በክብርህ ወጣሁኝ ዳገቱን አዝ፦ አሜን አሜን ብዬ ፊትህ እደፋለሁ ለመረጥከኝ ጌታ ምን እላለሁ አሜን አሜን አሜን ብዬ ፊትህ እደፋለሁ ለመረጥከኝ ጌታ ምን እላለሁ ያበጃጁኝ እጆችህ እንዴት የተዋቡ ናቸው የደሙትም እጆችህ እኔንም ያቀፉ ናቸው ዛሬም መጥተህ በእኔ ላይ ጌታዬ ሆይ ጫናቸው (2x)