ሁሉንም ትቼ እሮጣለሁ ያለኝንም ሁሉ አጣዋለሁ የሚጠቅመኝንም እተዋለሁ ብቻ አንድ ነገር አንድ ነገር እሻለሁ እርሱንም አውቃለሁ ሁሉም ቀርቶብኝ ቢገኝልኝ ኢየሱስ ነው ጉጉቴ የናፈቀኝ በእርሱ ተገኝቼ እርሱንም አግኝቼ ሌላ መሻት የለኝ የምራበው ኢየሱስ ዕንቁዬ ነው እርሱን ከማወቅ ጋር ምን ይወዳደራል ሁሉን እርግፍ አድርጐ አስትቶ ያስኬዳል ሽልማቴ ሌላ መች ለእኔ ሆነልኝ እርሱ ነው ኢየሱስ እኔን የወደደኝ (2x) ሽልማቴ ነህ የእኔ ጌታ ሽልማቴ ነህ የእኔ ኢየሱስ (2x) ሆነህ ተገኝተሃል በእኔ ዘንድ አንደኛ ሁሉንም አስናቅከኝ ኢየሱስ የእኔ እረኛ (2x) የከበረ የገነነ እኔ ምሻው ኢየሱስ ነው (፲2x)