ክብርህን ያዩ እንዴት ተገዙ! ከመንፈስ ረሀብ እንዴት ጠገቡ! ከዓለም ተለዩ አንተን ወደዱ የሙጥኝ ብለው ግርማህን አዩ አዝ፦ እኔም ፊትህ አዎ ዛሬ እወድቃለሁ ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን (2x) ቃልህን በግልጥ እንዲናገሩ ተሰበሰቡ አንተን ሊጠሩ ክብርህም ወርዶ አንደበት ነካ የመገለጥ ቃል አፋቸው ሞላ አዝ፦ እኔም ፊትህ ዛሬ እወድቃለሁ ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን (2x) ያላስተዋልኩት ከቶ ያላየሁት ድካሜ ይውጣ በሠማይ እሳት ልትሰራ ጌታ ክብርህን እንዳይ ይውረድ በእኔ ላይ ደመናህ ከላይ አዝ፦ እኔም ፊትህ ዛሬ እወድቃለሁ ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን (2x) ቀንና ሌሊት ፊትህ እወድቃለሁ ክብርህን እንዳይ እዋረዳለሁ ደግሞም ኢየሱስ እንደነበረ ትሁት አገልጋይ የተሰበረ አዝ፦ እኔም ፊትህ ዛሬ እወድቃለሁ ክብርህን ሳላይ መቼ እነሳለሁ ተጠማሁ ጌታ ሙሉ ግርማህን ጆሮ ያልሰማውን ዓይንም ያላየውን