ምሥጋና ይሞላ ሁልጊዜ አንደበቴ ለጸሎት ይንበርከክ እስኪዝል ጉልበቴ አፌም ይንቀሳቀስ ያውራ ስራህን ምላሴም ይናገር ይበል ክብርህን (2x) አዝ፦ መቼ ዝም ያሰኛል ብዙ ነው ውለታህ ለእኔ ያደረከው ድንቅ ተዓምራትህ ኦ ድንቅ ተዓምራትህ (2x) አጽናናህ አበረታህ ቁርጭምጪሚቴን እየሮጥኩኝ ላውራ ሜዳ ዳገቱን ይህ የመዳን ወንጌል ለዓለም ይዳረስ በሠማያዊው ጠል ነፍስ ሁሉ ይረስርስ (2x) አዝ፦ መቼ ዝም ያሰኛል ብዙ ነው ውለታህ ለእኔ ያደረከው ድንቅ ተዓምራትህ ኦ ድንቅ ተዓምራትህ (2x) ላላወቁህ ሁሉ ቀርበው ላልቀመሱ መናገር እንድችል ሙላኝ በመንፈስህ ሕይወቴ አርክቶህ ወዳንተ እስክደርስ ምስክር አድርገህ ለክብርህ አቁመኝ (2x) አዝ፦ መቼ ዝም ያሰኛል ብዙ ነው ውለታህ ለእኔ ያደረከው ድንቅ ተዓምራትህ ኦ ድንቅ ተዓምራትህ (2x)