ጽዋ ሲሞላ ሰዓቱ ሲደርስ የጌታ ሞገስ በእኛ ላይ ሲፈስ ከፍታውም ዝቅ ሸለቆውም ከፍ ካለ በኋላ ጌታ ይላል ከተፍ (2x) አዝ፦ በራሱ ምሎ በገዛ ክንዱ ጣልቃ የሚገባ ኧረ ማነው እርሱ እግዚአብሔር ነው እንጂ ቀን የሚቀጥረው ያልተጠበቀን ነገር የሚያደርገው (2x) ገና ብዙ አለ በመዝገቡ (2x) እርሱ ጌታዬ መሆኑን አይቼ እጮሃለሁኝ እጆቼን አንስቼ የማላቀውን ነገር የሚያሳየኝ እንደእግዚአብሔር ኧረ የት ሊገኝ (2x) አዝ፦ በራሱ ምሎ በገዛ ክንዱ ጣልቃ የሚገባ ኧረ ማነው እርሱ እግዚአብሔር ነው እንጂ ቀን የሚቀጥረው ያልተጠበቀን ነገር የሚያደርገው (2x) ገና ብዙ አለ በመዝገቡ (2x) ጌታ ጌታ ጌታ ነውና ስለቤቱ የሚቀና ቃል የገባውን ይፈጽማል ተስፋውንስ መቼ ያጥፋል (3x) ገና ብዙ አለ በመዝገቡ (2x) ገና ብዙ አለ (ብዙ አለ) ብዙ አለ (ብዙ አለ) ብዙ አለ በመዝገቡ (4x)