ከእንግዲህ ለማን ብዬ ለምን ብዬ አልሳሳም ለሕይወቴ ተስገብግቤ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ እንደሆነ አውቃለሁ እራሴንም እንደመስዋዕት ፉቱ አቀርባለሁ (2x) ለእግዚአብሔር ነው (ለእግዚአብሔር ነው) ለእኔ ሕይወት የማይቆጨኝ (የማይቆጨኝ) ብሰዋለት ለእግዚአብሔር ነው (ለእግዚአብሔር ነው) ለእኔ ሕይወት የማይቆጨኝ ብሰዋለት ዓይኖቼ በርተውልኝ ጌታን ሳየው ቸርነቱን ቀምሼ ሳጣጥመው ሌላው ነገር ሁሉ ይደበዝዝና እርሱ ብቻ ይሆናል ልቤን የሚሞላ (2x) ክብሩን ሳየው (ክብሩን ሳየው) ግርማውን ያስጥለኛል (ያስጥለኛል) ሁሉንም ክብሩን ሳየው (ክብሩን ሳየው) ግርማውን ያስጥለኛል ሁሉንም ክብሩን ሳይሆን ሞቱን የተመኙ የሄደበትን መንገድ ተረድተውት ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ሁሉንም ወርውረው እርሱን እርሱን ያሉት ከቶ ለምንድን ነው (2x) ያ ፍቅሩ ነው (ያ ፍቅሩ ነው) የሚያስጥለው ሌላ ነገር (ሌላ ነገር) የማያስመኘው ነው ሊያፈቅሩ ነው (ሊያፈቅሩ ነው) የሚያስጥለው ሌላ ነገር (ሌላ ነገር) አያስመኝም ለእግዚአብሔር ነው (ለእግዚአብሔር ነው) ለእኔ ሕይወት የማይቆጨኝ (የማይቆጨኝ) ብሰዋለት ክብሩን ሳየው ግርማውን ያስጥለኛል (ያስጥለኛል) ሁሉንም