Song Lyrics

ዙፋኑ ላይ

Pastor Mesfin Mamo
Shilimate Neh
አዝ፦ ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (2x) በደሌ እንደሙታን አድንዞኝ ሳለሁ በኢየሱሴ በኩል ወደአብ ዘንድ ገባሁ በሥጋዬ ምኞት እየኖርኩኝ ሳለሁ ከፍቅሩ የተነሳ ፀጋውን አገኘሁ አዝ፦ ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (2x) ቸርነቱን ሊያሳይ ከእርሱ ጋር አስነሳኝ ነላይኛው ስፍራ በቀኙ አስቀመጠኝ እንግዲህ አልመካም ከስራዬ አይደለም በእምነት የተገኘ ስጦታ ነው ይህ . (1) . አዝ፦ ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (2x) ጌታዬ ኢየሱስ አደንቅሃለሁ በአንተ ውብ ፍቅር ተነድፌያለሁኝ (2x) አዝ፦ ዓይኖቼ አይተውህ እጅጉን ፈዘዙ የፍቅርን እንባ አወጡ ከቶ ሳይታዘዙ ነፍሴም አልቻለችም መድሃኒቷን ስታይ ከጐኑ ስትሆን ከዚያ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ዙፋኑ ላይ ከዚያ ዙፋኑ ላይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection