ድምጹን እያሰማ ቀኔን የሚያበራ አላውቅም እንደጌታ መጪውንም ዘመን ቀድሞ የሚናገር አላየሁም ከእርሱ በቀር ለዘመኔ ባዳ እንዳልሆን እንግዳ ሚስጢሩን ይገልጸዋል በጓዳ አምላኬ ኦ እንዴት እንዴት ልዩ ነህ (2x) አዝ፦ አልወጣም ከፊትህ (ከፊትህ) አይለየኝ መንፈስህ (መንፈስህ) አላማዬ አንተ ነህ መኖሪያዬ ሕይወት ትርጉም ያለው በአንተ ነው ጌታዬ (2x) ድምጽህን ሰምቼ እረፍት ተሞልቼ ኖሬያለሁ ጸንቼ ከአንተ ተጠግቼ ልብህን አግኝቼ ቀረሁኝ ገብቼ ፊትህ እቆማለሁ ኃይልህን አያለሁ አልወጣም ከክብርህ ውርስ . (1) . ወስኛለሁ አምላኬ ሆ እንዴት እንዴት ልዩ ነህ (2x) አዝ፦ አልወጣም ከፊትህ (ከፊትህ) አይለየኝ መንፈስህ (መንፈስህ) አላማዬ አንተ ነህ መኖሪያዬ ሕይወት ትርጉም ያለው በአንተ ነው ጌታዬ (2x) እኔስ አውቄያለሁ ሚስጥሩን አግኝቻለሁ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ መነሻ መድረሻም አንተ ነህ ብያለሁ ክብርህን ሳይ ጌታ እጠግባለሁ (2x) አምላኬ ሆ እንዴት እንዴት ልዩ ነህ (2x) አዝ፦ አልወጣም ከፊትህ (ከፊትህ) አይለየኝ መንፈስህ (መንፈስህ) አላማዬ አንተ ነህ መኖሪያዬ ሕይወት ትርጉም ያለው በአንተ ነው ጌታዬ (2x) አልወጣም ከፊትህ አልወጣም ከፊትህ (አልወጣም ከፊትህ) (3x) ከማደሪያህ ከመቅደስህ አልወጣም ከፊትህ