በፊትህ መሆን ነው ደስታዬ ድምጽህ ጣፋጭ ሆናል ለጆሮዬ ከአንተ ሌላ የለም የሚያረካኝ እንተ ነህ እግዚአብሔር ምተመችኝ እንተ ነህ እግዚአብሔር ምተመችኝ ምሥጋናዬ ለአንተ ለጌታዬ አምልኮዬ ለአንተ ለጌታዬ ዝማሬዬ ለአንተ ለጌታዬ አመልክሃለሁኝ በምሥጋና አዜምልሃለሁ በምሥጋና አቀኝልሃለሁ በምሥጋና አንተን እንጂ ምንም አልፈልግም እንዳንተ የሚሆን ማንም የለም ለኔ እግዚአብሔር ወዳጄ ነህ በዚህ ደስ አለኝ ላመስግንህ በዚህ ደስ አለኝ ላመስግንህ የሚጠቅመኝ የለም በዚህች ምድር ከአንተ በስተቅር ከእግዚአብሔር አስፍቼ እሄዳለሁ በመንገድህ ተድላ ሆኖልኛል ትህዛዝህ ሰላም ሆኖልኛል ትህዛዝህ ነፍሴ ዝም ብለሽ አመስግኚው እግዚአብሔር አምላክሽን እርሱን ወደጂው ልጅን በመሰዋት አቅርቦሻል በፍቅሩ ሁልግዜ ያረካሻል በፍቅሩ ሁልግዜ ያረካሻል