Song Lyrics

ክብርህን አይ ዘንድ

Netsanet Assefa
Alegn Bizu Misgana
ክብርህን አይ ዘንድ እሻለሁ ረሃቤ ጥማቴ ይኸው ነው ሞገስ ካገኘሁኝ በፊትህ ለምኜ እንድቀበል ከፈቀድህ እንድ ጥያቄ ነው እኔ ያለኝ ጌታዬ ክብርህን አሳየኝ ክብርህን ያዩ አባቶቼ ለአንተ የኖሩትን ኑሮ አይቼ እየዋለ እያደር የጠማኝ ክብርህ ነው ጌታ የራበኝ ምን ዓይነት እሳት ነው ሙሴ ያየው ምን ዓይነት ብርሃን ነው ጳዎሎስ ያየው ምንድነው ጌታዬ የነካቸው ለአንተ እንዲኖሩ ያረጋቸው ደስታን ነው ለኔ ያሰበው ሰላምን ነው ለኔ ያሰበው ሊያድነኝ ነው ጌታ የመጣው ሊያድነኝ ነው ጌታ የመጣው ለዚህ እኮነው ነፍሱን የሰጠው ለዚህ እኮ ነው ነፍሱን የሰጠው አመልከዋለሁ ጌታዬን አመልከዋለሁ አምላኬን አመልከዋለሁ ጌታዬን አመልከዋለሁ አምላኬን ባወራ ስለእርሱ ብናገር ስለእርሱ ባስብም ስለእርሱ ብተርክ ስለእርሱ ይሄ ነው ሃሳቡ የእርሱ የንጉሱ ባወራ ስለእርሱ ብናገር ስለእርሱ ባስብም ስለእርሱ ብተርክ ስለእርሱ ይሄ ነው ሃሳቡ የእርሱ የንጉሱ ውበቱን ላይ ነው ጥሪዬ ግርማውን ላይ ነው ጥሪዬ ውበቱን ላይ ነው ጥሪዬ ግርማውን ላይ ነው ጥሪዬ ባወራ ስለእርሱ ብናገር ስለእርሱ ባስብም ስለእርሱ ብተርክ ስለእርሱ ይሄ ነው ሃሳቡ የእርሱ የንጉሱ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection