አለኝ ብዙ ምሥጋና ለአንተ አለኝ ብዙ ምሥጋና አምላኬ ነህና እጅህ ሰርታኛለች ተመስገን እፍ ብለህብኝ እስትንፋስህን ሕያው ነፍስ ያለብኝ አደረከኝ ተመስገን አምላኬ አበጀኽኝ በእናቴ ማህጸን ገና ሳለሁ በአንተ በአምላኬ ተለየሁ ሳላውቅህ አውቀኸኝ ላዳንከኝ ለውለታህ ብዙ ምሥጋን አለኝ በመሰዋት ጻድቁን ልጅህን ገለጽክልኝ እኔን መውደድህን የእዳ ጽህፈቴን ደምስሰኽው ሕይወቴን የሞላው ምሥጋናህ ነው ህልናዬን በደምህ ቀድሰህ መንፈስክህ ሞላኸኝ እንዳመልክህ በቅዱሳን መሃል አቁመኸኝ የከበረን መዝሙር አዘመርከኝ በሥጋዬ ከከበኝ ሃጥያት አስጣልከኝ አድርገህልኝ ምህረት ታማኙና ኃይለኛው ክንድህ ታድጐኛልና ላመስግንህ በራሴ ስራ እኔን እያሳፈረክ ሽታዬን ጠረኔን እየቀይርክ በቃልህ ሰይፍ እየቆረጥከኝ ያለጠባስ ቁስሌን ፈወስከኝ አለኝ ብዙ ምሥጋን ለአንተ አለኝ ብዙ ምሥጋና ሰሪዬ ነህና