ራስህን መስዋት አርገህ ስለእኛ ታርደሃል ለአምላክህ አዲስ ሕዝብን በደምህ ዋጅተሃል መንግሥትና ካህናት ለአባትህ አዘጋጀህ አምልኮ ውዳሴ ምሥጋና ይብዛልህ ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ እንዳተ ያለ አዳኝ አልተገኘምና ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና ይገባሃልና ከንፈሮችህ ጠቢብ በዕውቀት የላቁ ጻድቅ ሆይ በዕውቀትህ ብዙዎች ጸደቁ ለእግዚአብሔር ማደሪያ ቤትን ሰራህለት አብም በአንተ ስራ ደስ ተሰኘበት ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ እንዳተ ያለ ጥቢብ አልተገኘምና ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና ይገባሃልና ነግስታት ኃያልን ጠቢባንም ጭምር ጌታ ዝቅ በለው ይስጡ ለአንተ ክብር ጐልማሶች ቆንጆዎች ሽማግሌዎች ይምጡ ለታላቅነትህ ክብርን ለአንተ ይስጡ ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ እንዳተ ያለ ጌታ አልተገኘምና ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና ይገባሃልና ከመላእክት በላይ ከነቢያት በላይ ከሊቀ ካህናት ከአባቶችም በላይ ተሹመህ በአብ ቀኝ ኢየሱስ ተቀምጠሃል አምልኮ ውዳሴ ስግደት ይገባሃል ምሥጋና ይብዛልህ አምልኮ ይብዛልህ ሌላማ ምን አለ ለአንተ የሚሰጥህ እንዳተ ያለ አምላክ አልተገኘምና ኢየሱስ ሆይ ይብዛልህ አምልኮ ምሥጋና ይገባሃልና